ለመደበኛ መርሃ ግብር ድህረ-ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

                                          ሐምሌ 28ቀን 2014 ዓ.ም

ማስታወቂያ

ለመደበኛ መርሃ ግብር ድህረ-ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ ግብር በሁለተኛ ዲግሪ እና በሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የመግቢያ መስፈርቱን የሚያሟሉ እና መማር ለሚፈልጉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 10 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ ለአዲስ አመልካቾች ከተዘጋጀው ድረ ገጽ https://bdu.edu.et/graduatapp/የማመልከቻ ቅጹን በማውረድ (Download) በማድረግና በመሙላት ከላይ በተገለፀው ድረ-ገጽ online ወይም በአካል ትምህርቱ ወደሚሰጥበት የአካዳሚክ ክፍል ሬጅስትራር በመገኘት ማመልከት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለምዝገባ መሟላት የሚገባቸውን ዶክመንቶች፤ ትምህርት የሚሰጥባቸውን የሙያ መስኮች፤ ለማመልከቻ (application fee) የሚከፈልባቸውን የዩኒቨርሲቲው የባንክ ቁጥሮችን እና የማመልከቻ ፎረሙን ከማመልከቻ ድረ-ገጹ https://bdu.edu.et/graduatapp/ ማግኘት ይችላሉ::

ማሳሰቢያአመልካቾች

1ኛ ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት (Official Transcript) ማስላክ ይኖርባቸዋል፡፡

2ኛ ዩኒቨርሲቲው የሚያዘጋጀውን የመግቢያ ፈተና ወስደው ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ፈተና የሚሰጥበት ቀን በውስጥ ማስታወቂያ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ እና የፌስቡክ ገጽ ወደፊት ይገለፃል፡፡

stamp13ኛ ከዚህ በፊት ለመማር ተመዝግበው ባቋረጡበት የትምህርት መስክ በተመሳሳይ የቅበላ ዓይነት መመዝገብ አይቻልም፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት

Thursday, August 4, 2022 - 13