ለነባርና አዲስ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ

ታህሳስ 26 ቀን 2016 ዓ.ም
ለነባርና አዲስ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ
በ2016 የትምህርት ዘመን ትምህርት ሙሉ በሙሉ ሳይጀምሩ የቆዩ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ከጥር 1 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ባሉ ሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎችን ጠርተው የመማር ማስተማር ስራቸውን እንደሚጀምሩ በትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ መሰጠቱ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም፤
1. የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ1ኛ ዓመት ጀማሪ መርሃ ግብር 2ኛ ወሰነ ትምህርት ተማሪዎች እንዲሁም የ3ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ነባር መደበኛና የማታ ቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ከጥር 15 እስከ ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ፣
2. በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ/ም አዲስ የተመደባችሁ የጀማሪ መርሐ ግብር (Freshman) (ተማሪዎች እና የማካካሻ መርሐ ግብር (Remedial Program) ተማሪዎች እንዲሁም በ2015 ዓ.ም የማካካሻ መርሐ ግብር (Remedial Program) ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያላችሁ ተማሪዎች ከጥር 21 እስከ ጥር 23 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በዩኒቨርሲቲው በአካል በመገኘት ከዚህ በታች በተገለፁት ግቢዎች እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፤
1ኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ፣
• ብርድ ልብስ፤ አንሶላ፤ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፤
• የ8ኛ ክፍል ካርድ፤ ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት እና የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣
• 4 ጉርድ ፎቶ ግራፍ ይዛችሁ መምጣት ይኖርባችኋል፡፡
2ኛ በተለያየ ምክንያት ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ እና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች የምትገቡበት ባች በሚመዘገቡበት ቀን ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
Friday, January 5, 2024 (All day)