የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ10 ዓመቱ ስትራቴጅክ ዕቅድ ውይይት

የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ10 ዓመቱ ስትራቴጅክ ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ
==============================================
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በኮሌጁ የ10 ዓመት ስትራቴጅክ እቅድ ዙሪያ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች እና መንግስታዊ ከሆኑና መንግስታዊ ካልሆኑ አጋር አካላት የተውጣጡ ባለሙያዎች በተገኙበት ሰፊ ውይይት አካሂዷል፡፡
 
በፕሮግራሙ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፕ/ር የሺጌታ ገላው ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የ10 ዓመ ትመሪ ዕቅዱ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን ራዕይና ተልኮ ግምት ውስጥ በማስገባት መቅረቡን አመላክተዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ በእቅዱ ዝግጅት ላይ የተሳተፉትን የዝግጅት ቡድን አባላት ለነበራቸው ሙያዊ አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር እሰይ ከበደ በበኩላቸው ተቋሙ ገና በቅርቡ የተቋቋመ ቢሆንም እያስመዘገበ ያለው ውጤት ከሀገርም አልፎ በአፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪ እየሆነ ይገኛል ብለዋል፡፡
 
የ10 ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅዱ በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሀኪም በሆኑት ዶ/ር ወንድማገኝ እምቢያለ የቀረበ ሲሆን በውይይቱ እንደ ጭብጥ ከተነሱት ርእሶች ውስጥ የሚከተሉት ተካተዋል፡-
1. Excellence in clinical and community service outcome.
2. Excellence in academic quality and relevance.
3. Excellence in Research and Technology Transfer.
4. Excellence in leadership and Governance, and Institutional capacity.
5. Excellence in communication and partnership.
በእለቱም ሁሉም ታዳሚዎች በቡድን ተወያይተው በርካታ ሃሳቦች በእቅዱ እንዲካተቱበት ተደርጓል፡፡