ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ

ቀን፡ 29/12/2012 ዓ.ም

ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ‘’በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራሮችና አስተዳዳሪዎችን ምርጫ፣ ሹመት/ምደባ ለመደንገግ ባወጣው መመሪያ 002/2009 መሰረት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ‘’የመካከለኛ አመራር ምርጫ፣ ሹመት/ምደባ መመሪያ ቁጥር 002/2010’’ በዩኒቨርሲቲው ሴኔት አጽድቆ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ዩኒቨርሲቲው ለScience College የጥራት ማረጋገጫ አስተባባሪ/ Quality Assurance Coordinator የነበሩት ኃላፊነታቸውን በመልቀቃቸው በመመሪያው በወጣው መስፈርት መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመሾም ይፈልጋል፡፡

ክፍት የኃላፊነት ቦታ፡ የጥራት ማረጋገጫ አስተባባሪ/ Quality Assurance Coordinator

 

የማወዳደሪያ መስፈርት ፡-

1ኛ. የትምህርት ደረጃ፡- ሌክቸረርና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት

 

2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት እርከን ያገለገለ/ች እና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች፤

 

3ኛ. በሚያመለክቱበት አካዳሚክ ክፍልና ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የመማር ማስተማር፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም ተያያዥ ሂደቶችን ጥራት በማረጋገጥ በኩል አካዳሚክ ክፍሉ ሊሄድባቸው ስለሚገቡ ተጨባጭ መንገዶች ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪ መስጠት የሚችል/ምትችል

 

4ኛ. የአካዳሚክ ክፍሉ ማህበረሰብ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለጻ መስጠት የሚችል/ምትችል፤

 

አመልካቾች፡-

 

ይህ ማስታወቂያ በዩኒቨርሰቲው ድህረ-ገጽ፣ ፌስቡክና ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከተገለጸበት ነሀሴ 29/2012 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርሰቲ አጠቃላይ የጥራት አስተዳደር ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት (ጥበብ ህንጻ 3ኛ ፎቅ፤ ቢሮ ቁጥር 303) ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

 

ለበለጠ መረጃ፡ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች 0918769703 ወይም 0922117371 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡