የውስጥ የስራ ማስታወቂያ

ቀን፡ 06/01/2013 .

የውስጥ  የስራ ማስታወቂያ

-------------------------------------

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛና ዝቅተኛ አመራር ምርጫ፣ ሹመት/ ምደባ ለመደንገግ በወጣው የሴኔት (ማሻሻያ) መመሪያ ቁጥር 05/2012 መሰረት ብቁ አመልካቾችን ከዩኒቨርሲቲው አወዳድሮ ለስፖርት አካዳሚ ዲን ለመመደብ ማስታወቂያ ማውጣት አስፈልጓል፡፡

 

የማወዳደሪያ መስፈርት

 

1ኛ. የትምህርት ደረጃ፡ ማስተርስ ዲግሪና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት፤

 

2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት እርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች፤

 

3ኛ. በስፖርት አካዳሚና በዩኒቨርሲቲው ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትሃዊነት፣ ጥራት፣ ተገቢነትና ዓለምአቀፋዊነትን ለማሳካት፣ አካዳሚክ ክፍሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለማቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል፤

 

4ኛ. የአካዳሚክ ክፍሉ ማህበረሰብ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለጻ መስጠት የሚችል/ምትችል፤

 

አመልካቾች፡-

 

ይህ ማስታወቂያ በዩኒቨርሰቲው የማስታወቂያ ሰሌዳና ድህረ-ገጽ ከተገለጸበት ከመስከረም 07 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የሥራ ቀናት የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

 

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ